MRKUZinitiative
"Only a life lived for others is a life worth living"
ምርኩዞች ነን

ፕሮጀክቶች

ፕሮጀክት ጠያቂ
ፕሮጀክት ጠያቂ በሆስፒታል ቆይታቸው ወቅት ታካሚዎችና አስታማሚዎቻቸው የሚያጋጥማቸውን ሥነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ለመቀነስ የሚሠራየምርኩዝ አካል ነው። የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በሙሉ መፍታት ባንችል እንኳ አብሮ በመሆን፣ ታሪካቸውን በማዳመጥና ደግነትን በተግባር በማሳየት የከበዱ አፍታዎችን ማቅለል እንደሚቻል እናምናለን። በተመሳሳይ መልኩ ጠያቂ ለቅድመ-ሕክምና (Premedical) እና ለቅድመ-ክሊኒካል (Preclinical) ተማሪዎች ወደ ክሊኒካዊ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ቀድመው ከሆስፒታሉ ድባብ ጋር እንዲላመዱ፣ ልምድ እንዲቀስሙና በራሳቸው የመተማመን ስሜት እንዲገነቡ ዕድል ይፈጥራል።...

ፕሮጀክት ጠቋሚ
የጠቋሚ ፕሮጀክት የተመሰረተው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ ሰፊ ግቢ ውስጥ ብዙ ታካሚዎች እና አስታማሚዎች የሚያጋጥሟቸውን ቦታዎችን ደልጎ የማግኘት ችግሮች ለመፍታት ነው። ትክክለኛውን ቢሮ ወይም የሕክምና ክፍል ፈልጎ ማግኘት ግራ የሚያጋባና ጊዜ የሚወስድ በሊሆን ስለሚችል፣ በተለይም ለተመላላሽ ታካሚዎች የሕክምና አገልግሎታቸው እንዲዘገይ እና በአጠቃላይ በሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ ያላቸው እርካታ እንዲቀንስ ያደርጋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ፕሮጀክቱ ተገልጋዮችበሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ በቀላሉ እንዲንቀሳቀሱ የሚያግዝ የተቀናጀ የመመሪያና የጥቆማ አገልግሎት ይሰጣል።...

ፕሮጀክት መድኃኒት
ፕሮጀክትመድኃኒት ታካሚዎች ከሚጋፈጡባቸው እጅግ ፈታኝ ችግሮች መካከል አንዱ የሆነውን ማለትም የታዘዙ መድኃኒቶችንና አስፈላጊ የሕክምና ቁሳቁሶችን የመግዛት አቅም ማጣትን ለመፍታት የተጀመረ ነው። ፕሮጀክቱ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከሚገኘው የማኅበራዊ አገልግሎት ቡድን ጋር በቅርበት በመሥራት የገንዘብ ችግር ያለባቸውን ታካሚዎች የሚለይ ሲሆን፣ የሚያስፈልጋቸውን ሕክምና እንዲያገኙም የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል። በተጨማሪም ታካሚዎች ሕክምናቸውን በአግባቡና ሳያቋርጡ እንዲከታተሉ በማገዝ በሆስፒታሉ ሀብትና ንብረት ላይ የሚፈጠረውን ጫና ይቀንሳል።...
ምርኩዝ እስካሁን





ምርኩዝ ክፍላት
ምስክርነት
Are you ready to improve the lives of patients through compassionate support?
ለጋዜጣችን ይመዝገቡ
ከምርኩዝ ኢኒሼቲቭ አዳዲስ ዜናዎችን እና መረጃዎችን በወቅቱ ያግኙ





